ስለ ቤተክርስትያናችን

ልደታ ማርያም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በቶሮንቶ

ልደታ ማርያም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በቶሮንቶና በአካባቢው የሚገኙ ካቶሊክ ኢትዮጵያዊያንን በዋናነት የምታገለግል ቤተክርስትያን ስትሆን የምትደዳረውም በቶሮንቶ ሃገረ ስብከት ስር ነው።

ክቡር አባ ኢሳያስ ዱላ መሪ ካህን ሆነው ለማገልገል ከመጡበት እና ቤተክርስቲያናችን ከተመሠረተችበት  ከ2009 ጀምሮ ቤተክርስቲያናችን በመንፈሳዊ አገልገሎትና በምዕመናን ቁጥር እያደገች የመጣች ሲሆን የምዕመናን ምክር ቤቱም ከአባ ኢሳያስ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡

ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ወቅት በቶሮንቶ ዳቭን ፖርት ሮድ ላይ በምትገኘው በቅድስት ማርያም ፖሊሽ ቤተክርስቲያን ከፖሊሽ ካቶሊካዊያን ወንድሞችና እህቶች ጋር በመዳበል የተሟላ ቅዳሴና መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች።ለልጆቻችንም የካቶሊክን ስርዓት በተከተሉ መንፈሳዊ መርህ ታንጸው የሚያድጉበት አመቺ ቦታ ሆናለች፡፡

የቤተክርስቲያናችንም ዓመታዊ ክብረ በዓል (ልደታ ማርያም) በየአመቱ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ከኤርትራዊያን ኪዳነ ምሕረት ካቶሊካዊያን ወንድሞችና እህቶች፣ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ወዳጆቻችንና እንግዶቻችን ጋር በመሆን በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡

 

ልደታ ማርያም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በቶሮንቶ
1996 Davenport Rd, Toronto, ON  M6N 1C4
ስልክ ቁጥር:. (647) 995-8606 / ኢ-ሜይል: lmethiocatholic@gmail.com


በህዝብ ትራንስፖርት ለመምጣት
ሁለት አማራጭ:

  1. ከዳንዳስ ዌስት ሰብዌይ ጣቢያቁጥር 168 ሲሚንግተን አውቶብስ ይወስዱና “ኦስለር’ ማቆምያ ላይ ወርደው በግምት 2 ደቂቃ ወደ 1996 ዳቨን ፖርት ሮድ በእግር ይሄዳሉ። 

  2. ከስፐዳይና ሰብዌይ ጣቢያ፣ ቁጥር 127 ሲሚንግተን አውቶብስ ይወስዱና “ኦስለር’ ማቆምያ ላይ ወርደው በግምት 2 ደቂቃ ወደ 1996 ዳቨን ፖርት ሮድ በእግር ይሄዳሉ።