ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ አባ ደጀኔ ሂዶቶን አዲሱ የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብለው መሰየማቸውን ቫቲካን ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. አውጇል። 

ክቡር አባ ደጀኔ ሂዶቶ እ.ኤ.አ መጋቢት 21 ቀን 1972 ዓ.ም. በሶዶ ስባዬ የተወለዱ ሲሆን የመጀምሪያ ዲግሪያቸውን በሶሾሎጂ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የማስተርስ ዲግሪያቸውን ደግሞ በኦታዋ ካናዳ ቅዱስ ጳውሎስ ዩኒቨርስቲ በማህብረሰብ ሥነምግባር ተቀብለዋል። ክቡር አባ ደጀኔ እ.ኤ.አ ነሐሴ 9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በቅዱስ ፍራንቼስኮስ ነገረ መለኮት ትምህርት ቤት የፍልስፍና እና የነገረ መለኮት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።  

ክቡር አባ ደጀኔ ሂዶቶ በሶዶ ሀገረስብከት በሚገኘው የዱቦ የእመቤታችን ሉርድ ማሪያም ቁምስና ቆሞስ፣ በአዲስ አበባ ሀገርስብከት መድሃኔዓለም ቁምስና የአለም ዓቀፍ ካቶሊካውያን ማህበር በኢትዮጵያ አጋዥ ቻፕሊን፣ በሶዶ የሚገኘው የአባ ፓስካል የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ኃላፊ እ.ኤ.አ ከ2023 እስካሁን የሶዶ ሀገረ ስብከት የሐዋርያዊ ቢሮ ኃላፊ እና ካፑቺን ማህበር በኢትዮጵያ የኪዳነ ምህረት ገዳም ኃላፊ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ደስታውን እየገለጸ ለክቡር አባ ደጀኔ የተባረከ የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።

Previous
Previous

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የ2016 ዓ.ም. የፍልሰታ ፆም መግቢያን አስመልክተው ያስተላለፉት መልእክት 

Next
Next

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በቫቲካን አጸድ ውስጥ 500 ዓመት ያስቆጠረ ንብረት እንዴት አፈራች?